minuttest

በኤች.አይ.ቪ የተያዙ ወይም በኤች.አይ.ቪ መመርመር ለሚፈልጉ ሁሉ የምናቀርባቸው አገልግሎቶች

በኤች.አይ. የተያዙ ወይም በኤች.አይ. መመርመር ለሚፈልጉ ሁሉ የምናቀርባቸው አገልግሎቶች፡

OSLOTRONDHEIMBERGEN

ኤች.አይ. ምንድነው?
ኤች.አይ.ቪ ምህጻረ ቃል ሲሆን የሰው ልጅ በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም ማለት ነው፡፡ ከአንድ ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በመፈፀም ሊተላለፍቦት የሚችሉት ህመም፣ እናቶች ልጅ በሚወልዱበት ወይም ጡት በሚያጠቡ ግዜ ወደ ልጆች ሊያስተላልፉት ወይም በበሽታው ካለ ሰው በደም አማካኝነት ሊተላለፍ የሚችል ነው፡፡ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ኤች.አይ.ቪ ሊያዙ የሚችሉ ሲሆን ከየትኛውም ሀገር ቢመጡም ሆነ ከማን ጋር ወሲብ ቢፈጽሙ በህመሙ ሊያዙ ይችላሉ፡፡ ያለ መድሃኒት በጣም ሊታመሙና ሊሞቱ ይችላሉ፡፡ በኤች.አይ.ቪ የተያዙ ሁሉ በኖርዌይ ውስጥ ነፃ መድኃኒት ማግነኘት ይችላሉ፡፡ መድሃኒቱን ከወሰዱ ጤናማ እና መደበኛ ኑሮ ለመኖር እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን በኤች አይ ማስያዝ አይችሉም፡፡ ጥገኝነት ጠያቂ ከሆኑ ኤች.አይ.ቪ ቢኖርቦትም ሆነ ባይኖርቦት ማመልከቻዎ ላይ ተጽእኖ አይኖረውም፡፡ ኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ አንድ አይነት አይደሉም፡፡ በኤች.አይ.ቪ የተያዙ ከሆነ መድሃኒት እያገኙ መደበኛ ኑሮን መኖር ይችላሉ፡፡ ኤድስ ኤች.አይ.ቪ ካለብዎት እና መድሃኒቱን ካልወሰዱ ሊይዞት የሚችል በሽታ ነው፡፡ መድሃኒት ካልወሰዱ በኤድስ ይሞታሉ፡፡ 

ኤች.አይ. እንዴት ይተላለፋል?

 • ኤች.አይ. ካለበት ሰው ጋር ወሲብ ከፈጸሙና ኮንዶም ካልተጠቀሙ ከሆነ በኤች.አይ. ሊያዙ ይችላሉ፡፡
 • ኤች.አይ. ካለበት ሰው ጋር ተመሳሳይ መርፌን የሚጠቀሙ ከሆነ በኤች.አይ. ሊያዙ ይችላሉ፡፡
 • ነፍሰ ጡር እናት ኤች.አይ. ካለባት እና በየቀኑ የኤች.አይ. መድሃኒት የማትወስድ ከሆነ ህፃኑ በኤች.አይ. ሊያዝ ይችላል፡፡
 • በአንዳንድ ሀገሮች ደም በመስጥ (ግን በኖርዌይ ውስጥ አይደለም)፡፡

ኤች.አይ. እንዴት አይተላለፍም?

 • ኤች.አይ. ያለበት ሰው በየቀኑ መድሃኒቱን የሚወስድ ከሆነና መድሃኒቱ በትክክል የሚሰራ ከሆነ ኤች.አይ.ቪን አያስተላልፍም፡፡
 • ኤች.አይ. በምራቅ፣ በእንባ ወይም በሽንት ውስጥ አይገኝም፡፡
 • በአንድ ሰው አብሮ  በመሆን ወይም ከጎረቤቶ ከጓደኞች ወይም ከቤተሰብ ጋር በየቀኑ በመገናኘቱ በኤች.አይ. አይያዝም፡፡
 • ምግብ፣ መጠጥ፣ መጸዳጃ ቤት ወይም ገላ መታጠቢያን ቢጋሩ በኤች.አይ. አይያዙም፡፡
 • ሌሎች ሰዎችን ቢስሙ ወይም ቢነኩ በኤች.አይ. አይያዙም፡፡
 • ኤች.አይ. ከእንስሳት አይተላለፍም፤ ለምሳሌ፡ቢንቢዎች
 • PrEP ኤች.አይ. እንዳይያዙ የሚያደርግ መድሃኒት ነው፡፡ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያለው ወሲባዊ ግንኙነት ካለዎት ይህንን መድሃኒት ከሐኪምዎ ማግኘት ይችላሉ፡፡ እባክዎ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት እኛን ያነጋግሩን

ለኤች.አይ. አንዴት ምርመራ ማድር እችላለሁ?

 • ኤች.አይ. ብዙውን ጊዜ ምልክቶች የሉትም፡፡
 • ኤች.አይ. መያዝዎን ማወቅ የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ የደም ምርመራ በማድረግ ነው፡፡
 • ለኤች.አይ. የደም ምርመራን GP ወይም በምርመራ ክሊኒክ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ውጤቱን ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ ያገኛሉ፡፡
 • እኛ ጨምሮ በርካታ ተቋማት – minuttest.no – ፈጣን ምርመራዎችን የሚያደርጉ ሲሆን እነዚህም ነፃ፣ ስሙ የማይጠቀስና ውጤቱንም ወዲያውኑ የሚሰጡ ናቸው፡፡

www.minuttest.no

የአንድ ደቂቃ ምርመራ በብዙ Kirkens Bymisjon’s  (የቤተክርስቲያን ከተማ ተልዕኮ) ማዕከላት በነጻ ሊያገኙት የሚችሉ የኤች.አይ.ቪ ፈጣን ምርመራ ነው፡፡ ውጤቱን ወዲያውኑ ያገኛሉ፡፡   

ስሙ የማይገለጽ

የአንድ ደቂቃ ምርመራዎት ስምዎን ወይም የት እንደሚኖሩ ለእኛ መንገር አያስፈልግዎትም። ምርመራው ስላደረገ ማንኛውም ሰው በእኛ ማዕከላት መረጃ አናስቀምጥም፡፡

ሚስጥራዊነት

እዚህ የሚሰራ ማንም ስለእርስዎ፣ ስለ ሙከራዎ ወይም ስለ ሌሎች ስለሚናገሩት ነገር ምንም ነገር እንዲናገር አይፈቀድለትም፡፡ ሚስጥራዊነት አስፈላጊ ነው እኛም በቁም ነገር እንመለከተዋለን፡፡

ነጻ

በእኛ ማዕከላት እኛን ለማነጋገር ወይም የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ለማድረግ ምንም ወጪ አይጠይቅም፡፡

ፈጣን ምርመራ

የሚከናወነው በጣት ላይ ሲሆን ወዲያውኑ ውጤቱን ያገኛሉ፡፡

መቼ መመርመር እችላለሁ?

ኤች አይ ቪን ተይዣለሁ ብለው ካመኑ በጣም ጥሩው ነገር በተቻለ ፍጥነት እኛን ማግኘት ነው፡፡ ምርመራው 99.6% አስተማማኝ ነው፣ ኢንፌክሽኑን ይይዛሉ ብለው ካመኑ ከ 12 ሳምንታት በኋላ ግን ኤች.አይ.ቪን ይይዛሉ ብለው ካመኑ ከ 3 ሳምንት በፊትም ውጤቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ኤች.አይ.ቪ አለብኝ ብለው ካሰቡ መመርመርና ለሰው መንገሩ ጠቃሚ ሀሳብ ነው፡፡ ስለዚህ በጣም ጥሩው ነገር 12 ሳምንታት ሳይያልፉ ወደ እኛ መምጣት ነው፡፡

በበሽታው ሊያዙ ከቻሉ 48 ሰዓታት በታች ከሆነ ሊወስዱት የሚችሉት ልዩ መድሃኒት አለ፡፡ ይህ የአከባቢዎ GP ሊረዳዎ የሚችል ነገር ነው፡፡ ራስዎን በኤች.አይ. የመያዝ አደጋ ላይ ከጣሉ  በተቻለ ፍጥነት ለአካባቢዎ GP እንዲደውሉ እንመክራለን፡፡


ምርመራው ኤች.አይ. እንደያዝኩ ካሳየ ምን ይፈጠራል?

Kirkens Bymisjon (የቤተክርስቲያኗ ከተማ ተልዕኮ) በአካባቢያቸው ካሉ ሆስፒታሎች ለዚ ተብለው ከተቀመጡ ሰራተኞች ጋር አብሮ የሚሰራ ሲሆን በፍጥነት የሆስፒታል ቀጠሮ ይሰጥዎታል፡፡ ነፃ መድሃኒት ያገኛሉ፡፡ Kirkens Bymisjon በተጨማሪም በኤች.አይ.ቪ ለተያዙ በሙላ በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡ 

ከኤች. አይ. ጋር መኖር ምን ይመስላል?

 • በአሁኑ ጊዜ ኤች.አይ. በሕይወትዎ ዘመንዎ በሙሉ አብሮት የሚኖር ሁኔታ ነው ማለት እንችላለን እንላለን፡፡
 • በሽታውን ለማስወገድ የሚረዱ መድኃኒቶች ወይም መንገዶች የሉም ነገር ግን ጥሩ መድሃኒት ማለት እርስዎ አይታመሙም ወይም አይሞቱም ማለት ነው፡፡
 • በኖርዌይ ውስጥ በኤች.አይ. የተያዙ ሰዎች በሙላ ነፃ መድኃኒት ያገኛሉ፡፡
 • በቀሪው የሕይወትዎ ዘመንዎ በሙሉ መድሃኒቱን በየቀኑ መውሰድ ይኖርብዎታል፡፡
 • መድሃኒቱን ከወሰዱና መድሃኒቱ በጥሩ ሁኔታ የሚሰራ ከሆነ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፉ አይችሉም፡፡
 • መድሃኒቱን ከወሰዱና መድሃኒቱ በጥሩ ሁኔታ የሚሰራ ከሆነ የጾታ አጋርዎን ወይም ህፃኑን ሳይበክሉ በተለመደው መንገድ ልጅ መፀነስ ይችላሉ ፡፡
 • ይህ ማለት ኤች.አይ. እንደሌለው ሰው ረጅም እና ጤናማ ሕይወት ሊኖርዎት ይችላል ማለት ነው፡፡ የወንድ ጓደኛ / የሴት ጓደኛ እና ልጆች፣ ሥራ ሊኖርዎት እንዲሁም መደበኛ እና ጤናማ ሕይወት መኖር ይችላሉ፡፡
 • በኖርዌይ በኤች.አይ. የተያዙ ወደ 4000 ያህል ሰዎች አሉ ፡፡ በሌላ አገላለጽ ኤች.አይ. ካለዎት እርስዎ ብቻዎትን አይደሉም፡፡ ወንድም ሴትም ቢሆን፣ ከየትኛው አገር ቢመጡ ወይም ከማን ጋር ወሲብ ቢፈጽሙ ማንም ሰው ኤች.አይ. ሊያዙ ይችላሉ፡፡
 • Kirkens Bymisjon በኤች.አይ. ለተያዘ ማንኛውም ሰው በመላው አገሪቱን ብዙ አገልግሎቶችን ይሰጣል በመሆኑም በጥሩ መድሃኒትም ቢሆን ከኤች.አይ. ጋር በቀላሉ መኖር ለማንም ቀላል እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ ለሚከተሉት አይነት አገልግሎቶች እኛን ሊያገኙን ይችላሉ፡
 • በኤች.አይ. ከተያዙ ወይም በኤች.አይ. ከተጠቁ ከአንድ ሰው ጋር ለመነጋገር እድሉን ማግኘት፡፡
 • ከኤች.አይ. ጋር መኖርን እንዴት እንደሚችሉ ትምህርቶች፡፡
 • በኤች.አይ. ከተያዙ ሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት፡፡

Kirkens Bymisjon’s ኤች.አይቪ.አገልግሎት:

OSLO:

 • ፈጣን የኤች.አይ. ምርመራነፃ፣ ስም የማይታወቅና ውጤቶቹ በአንድ ደቂቃ ውስጥ የሚደርሱ፡፡
 • ስለ ኤች.አይ.ቪምክርና መመሪያ መረጃ
 • ለስደተኞች፣ ለአዋቂዎችና ከኤች.አይ. ጋር ለሚኖሩ ልጆች የሚሰጠው ትምህርት፡፡
 • በኤች.አይ. ከተያዙ ሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር፡፡
 • ከኤች.አይ. ጋር ለሚኖሩ ሰዎች መኖሪያ፡፡

  

Aksept Oslo/ Minuttest Oslo (ተቀባይነትከኤች.አይ. ጋር ለሚኖሩ ሰዎች ማዕከል)

አድራሻHammersborg torg 3

ስልክ: +47 23 12 18 20

ኢሜል: firmapost.aksept@bymisjon.no

አስተርጓሚ ከፈለጉ የስልክ አስተርጓሚ በማዘጋጀት ልንረዳዎ እንድንችል አስተርጓሚ ያስፈልገናል የሚል ሰው በስልክ እንዲያነጋግርዎ እንመክራለን፡፡ 

TRONDHEIM:

 • ፈጣን የኤች.አይ. ምርመራነፃ፣ ስም የማይታወቅና ውጤቶቹ በአንድ ደቂቃ ውስጥ የሚደርሱ፡፡
 • ስለ ኤች.አይ.ቪምክርና መመሪያ መረጃ
 • በኤች.አይ. ከተያዙ ሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር፡፡

Aksept Trondheim/ Minuttest Bergen (ተቀባይነትና መቋቋምከኤች.አይ. ጋር ለሚኖሩ ሰዎች ማዕከል)  

አድራሻ: Bergljotsgate 4b, 7030 Trondheim

ስልክ: +47 47 47 33 05

ኢሜል፡ health@bymisjon.no

አስተርጓሚ ከፈለጉ የስልክ አስተርጓሚ በማዘጋጀት ልንረዳዎ እንድንችል አስተርጓሚ ያስፈልገናል የሚል ሰው በስልክ እንዲያነጋግርዎ እንመክራለን፡፡ 

BERGEN:

 • ፈጣን የኤች.አይ. ምርመራነፃ፣ ስም የማይታወቅና ውጤቶቹ በአንድ ደቂቃ ውስጥ የሚደርሱ፡፡
 • ስለ ኤች.አይ.ቪምክርና መመሪያ መረጃ
 • በኤች.አይ. ከተያዙ ሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር፡፡

Minuttest Bergen/ Aksept Bergen (ብዝሀ ምርመራ Bergen / ከኤች.አይ. ጋር መኖር)

አድራሻ: Kong Oscars gate 62

ስልክ: +47 971 11 876

ኢሜል: bergen@minuttest.no

አስተርጓሚ ከፈለጉ የስልክ አስተርጓሚ በማዘጋጀት ልንረዳዎ እንድንችል አስተርጓሚ ያስፈልገናል የሚል ሰው በስልክ እንዲያነጋግርዎ እንመክራለን፡፡  

እዚህ ስለ ኤች.አይ. የበለጠ ማንበብ ይችላሉ: